አጠቃላይ መግለጫ


የአንተርፕርነርሽፕ ልማት ማዕከል (ኢ.ዲ.ሲ) በንግድ ስራ ፈጠራ ማጎልበት መርሃግብር መዋቅር ስር የተቋቋመ ከፊል መንግስታዎ የሆነ ተቋም ነው፡፡ በመንግስት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ የተቀመጠውን የንግድ ስራ ፈጠራ (አንተርፕርነርሺፕ) ማጎልበት ግቦችን ዕውን ለማድረግ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት በከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር በመወከል ከተባበሩት መንግስታት የዕድገት መርሃግብር ጋር በመተባበር የአንተርፕርነርሺፕ ልማት መርሃግብር የተባለ የአንተርፕርነርሺፕ ፈጠራንና የንግድ ድርጅቶችን ዕድገት የሚያጎለብት ጅማሮ በየካቲት 2005 (በፌብሩዋሪ 2013) አዘጋጅቶ አስተዋውቋል፡፡

የአንተርፕርነርሺፕ ልማት ማዕከል (ኢ.ዲ.ሲ) በከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ውስጥ በፌዴራል የከተማ ስራ ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ስር የሚተዳደር የንግድ ስራ ፈጠራ ማጎልበት መርሃግብርን ተግባራዊ የሚያደርግ ተቋም ነው፡፡ የኢ.ዲ.ሲ ዋና ጽ/ቤት በአዲስ አበባ እና በክልል ቢሮዎች ማለትም በቢሾፍቱ፣ በሃዋሳ፣ በባህርዳር እና በመቐለ ይገኛሉ፡፡ የክልል ቢሮዎቹ በየክልላቸው የሚገኙ ሁሉም ከተሞችን ያገለግላሉ፡፡ መርሃግብሩ ዕድገት ተኮር የንግድ ድርጅቶችን እንዲሁም የንግድ ስራ ፈጠራ አቅም ያላቸውን ሰዎች፣ ስራ-አጥ ወጣቶችን እና ሴቶችን በአገር አቀፍ ደረጃ ለመለየትና የንግድ ስራ ፈጠራ ክህሎታቸውን እና በዘላቂነት ተፎካካሪና ትርፋማ የንግድ ስራዎችን እንዲያቋቁሙ የሚያግዙ የንግድ ስራ ፈረታ ክህሎችንና ብቃቶችን ለማዳበር/ለመጨመር የሚያስችላቸውን ቀጥተኛ ድጋፍ ለመስጠት ያለመ መርሃግብር ነው፡፡
.

መርሃግብሩ በ4 ምሰሶዎች ላይ የተዋቀረ ነው• ምሰሶ 1፡የንግድ ስራ ማጎልበት መርሃግብርን ግብ ለማሳካትና ስኬታማ ተግባራዊነት ለመቆጣጠር በአዲስ አበባ የአንተርፐርነርሺፕ ልማት ዋና ጽ/ቤት (ኢ.ዲ.ሲ ኢትዮጵያ) ምስረታ እንዲሁም የአራት በከፊል ራሳቸውን የቻሉ የንግድ ስራ ፈጠራ ማዕከላትን (የኢ.ዲ.ሲ ቢሮዎችን) አቅማቸውን ለመገንባት በአራት ክልሎች የማቋቋም ስራ ተሰርቷል፡፡ ይህ ስራ የመንግስት እና የግል ሴክተሩን የመካከለኛ እና አነስተኛ የንግድ ድርጅቶች ገቢያቸውን ለመጨመርና ለወጣቶችና ለሴቶች በተለየ ትኩረት የስራ ዕድል ለመፍጠር የተቀናጀ እገዛ ለመስጠት እንዲቻል ተቋማዊ አቅምን መጨመርን ያካትታል፡፡ በተጨማሪም ይህ ምሰሶ በተመረጡ የህዝብ ዩኒቨርሲቲዎች የንግድ ስራ ፈጠራ የልህቀት ማዕከላትን ማቋቋም.

•ምሰሶ 2፡ በመላ አገሪቱ የሚገኙ የጥቃቅን እና አነስተኛ የንግድ ድርጅቶች ስለ ንግድ ስራ ፈጠራ ያላቸውን ዕውቀትና ክህሎት በማበረታታት በንግድ ስራ ክህሎት ስልጠና፣ በአሰልጣኞች ስልጠና እና የንግድ ስራ አማካሪዎች ስልጠና አማካኝነት ያላቸውን የማደግ አቅም ዕውን ለማድረግና የለውጥ ሂደቱን ማፍጠን

• ምሰሶ 3፡ በወጣቶችና ሴቶች ለሚመሩ ድርጅቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት በተከታታይ የንግድ ስራ ማማከር አገልግሎት አማካይነት የአዳዲስ መካከለኛ እና አነስተኛ የንግድ ድርጅቶችን መደራጀት/መቋቋም ማገዝና በስራ ላይ የሚገኙትን ብዛት መጨመር

• ምሰሶ 4፡ የፖሊሲ መመሪያዎችን፣ ለመካከለኛ እና አነስተኛ የንግድ ድርጅቶች ዕድገት ማነቆ የሚሆኑ ተቋማዊና የቁጥጥር ስራዎችን ለመለየትና ለመፈጸም መንግስትን ማገዝ ፣ ለጥቃቅን አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ድርጅቶች ዕድገት የሚያግዙ ተስማሚ የሆኑ አዳዲስ ገንዘብ ነክ መገልገያዎች፣ ገበያ እና ቴክሎጂዎችን ማግኘት እንዲችሉ የባለድርሻ አካላትንና በትብብር የሚሰሩ አጋሮችን ተሳትፎ ማበረታታት/ምስተዋወቅ .
የመርሃግብሩ አጠቃላይ ዓላማ በጥምረት በሚሰጡ የንግድ ስራ ፈጠራ እንዲሁም የአስተዳደር ክህሎት ስልጠናዎች እና የተቀናጀ በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀና ሰፊ የንግድ ስራ ማማከር አገልግሎቶች አማካኝነት ስኬታማና ዕድገት ተኮር የንግድ ድርጅቶችን ማቋቋም የቻሉ ተጠሪ የሚሆኑ አገር በቀል የንግድ ስራ ሰዎችን በማጎልበት የጥቃቅንና አነስተኛ ደረጃ የንግድ ድርጅቶችን የማደግ አቅም በማውጣት ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት ነው፡፡

በአገሪቱ የዕድገት አጀንዳ ውስጥ የተካተተውን የንግድ ስራ ፈጠራ ራዕይ በመመልከት ኢ.ዲ.ሲ የሚከተሉትን ሰዎች ፍላጎት ለማሟላት በልዩ ሁኔታ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፡-:

• በመደበኛ የንግድ ስራ ዘርፍ ውስጥ ዕድገት ተኮር ድርጅቶችን የመፍጠርና የማቋቋም አቅም ያላቸው አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ድርጅቶች

• የግላቸውን የንግድ ስራ ለመጀመርና የግል ስራ ተቀጣሪነትን ለማጎልበት ፍላጎት ያላቸው የንግድ ስራ ፈጣዎች ይሆናሉ ተብለው የሚታሰቡ ሰዎች

• የግላቸውን የንግድ ስራ ለመጀመርና የግል ስራ ተቀጣሪነትን ለማጎልበት ፍላጎት ያላቸው የንግድ ስራ ፈጣዎች ይሆናሉ ተብለው የሚታሰቡ ሰዎች

 • መስፋፋትን/ማደግን የሚሹ መካከለኛ ደረጃ የንግድ ድርጅቶች


  • +251-115-571-150
  • Cette adresse e-mail est protégée contre les robots spammeurs. Vous devez activer le JavaScript pour la visualiser.
© 2022. All Rights Reserved. EDC-Ethiopia

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.