የንግድ ስራ ፈጠራ (የአንተርፕርነርሺፕ) ስልጠና ወርክሾፕ (ኢ.ቲ.ደብሊው)

የንግድ ስራ ፈጠራ (የአንተርፕርነርሺፕ) ስልጠና ወርክሾፕ (ኢ.ቲ.ደብሊው) ከኢ.ዲ.ሲ የንግድ ስራ ማጎልበቻ መርሃግብሮች ውስጥ በምሳሌነቱ የሚጠቀስ ነው፡፡ የኢ.ቲ.ደብሊው ስልጠና የሚከተለው ባህሪ ተኮር አካሄድ የንግድ ስራ ፈጠራ - ሊታዩ፣ ሊታወቁ፣ ሊተገበሩ እንዲሁም የንግድ ስራ ፈጣሪዎች በዕለት ተዕለት ህይወታቸው ሊያዳብሯቸው የሚችሉ የተለዩ(የተወሰኑ) ብቃቶች የማዳበር እና የትግበራ ውጤት መሆኑን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ የኢ.ቲ.ደብሊው ስልጠና የሰልጣኞችን ተነሳሽነት እና በራስ መተማመን በማጎልበት ለንግድ ስራ ፈጣሪዎች የንግድ ስራን በተለምዶ ብቻ በመስራት እና ዕድገት ተኮር ድርጅት በመገንባት መሀከል ያለውን ልዩነት ያሳያል፡፡          

ስልጠናው ከ50 በላይ በሚሆኑ የንግድ ስራ ፈጠራ ትግበራና ልምምድ እንዲሁም የብቃት ማረጋገጫ ወረቀት ባላቸው ናሽናል፣ ማስተር እና ኢንተርናሽናል አሰልጣኞች ይሰጣል፡፡ ስልጠናው 6 ቀናት እና 48 ሰዐታት የሚፈጅ ስልጠና ነው፡፡ ኢ.ዲ.ሲ ይህንን ስልጠና በተለያዩ የአገራችን ቋንቋዎች (በአማርኛ፣ በኦሮምኛ እና በትግርኛ) እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ይሰጣል፡፡  

 

የኢ.ቲ.ደብሊው ልዩ የስልጠና አሰጣጥ ዘዴ ሁሉም ሰው ውስጣዊ የመሻሻል ተነሳሽነት አለው በሚል መነሻ በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲው የስነልቦና ፕሮፌሰር ዴቪድ ማክሊላንድ በአውሮፓውያን አቆጣጠር በ1960ዎቹ መጨረሻ የተሰሩ ጥናቶችን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ስልጠናው የአዋቂ ሰዎች የመማር መርሆች ላይ መሰረት ያደረገ ተሳታፊ ተኮር፣ ተግባራዊ፣ የአመለካከትና የባህሪ ለውጥ የሚያመጣ ስልጠና ነው፡፡ አብዛኛው የስልጠና አካሄድ በተለያዩ ጥናቶች፣ በትምህርታዊ ጨዋታዎች፣ በሮል ፕሌይ፣ በልምምዶችን እና በልምድ መለዋወጫ መንገዶች አማካይነት የሚሰጥ ነው፡፡  

 

የኢ.ቲ.ደብሊው ስልጠና ቀጥተኛ ተጠቃሚዎች ጥሩ የሆነ የንግድ ውጤታማነት ያላቸው በስራ ላይ ያሉ አነስተኛ እና መካከለኛ ድርጅቶችን፣ ተስፋ ሰጪ የንግድ ስራ ሃሳብ ያላቸው የንግድ ስራ ፈጣሪ የመሆን አቅም ያላቸውን፣ እንዲሁም ተግባራዊ ሊሆንና ትርፋማ ሊያደርግ የሚችል የንግድ ስራ ሃሳብ ያላቸው አዲስ ጀማሪ ድርጅቶችን ያጠቃልላል፡፡ በኢ.ቲ.ደብሊው ስልጠና ወቅት የሚጎለብተው የግለሰቦች ዕድገት የአነስተኛ እና መካከለኛ ድርጅቶችን ዕድገት፣ አገራትን ተሻግረው የሚሰሩትን ጨምሮ ከትልልቅ ድርጅቶች ጋር የሚደረግ ትስስርን፣ የስራ ፈጠራን፣ የመዋዕለ ነዋይ ፍሰት ዕድገትን፣ እንዲሁም አካባባቢያዊ የምጣኔ ሃብት ዕድገትን ለማምጣት የመሪነት ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል፡፡

 

በስልጠናው የሚጠበቅባቸውን አስፈላጊ ሁኔታዎች በብቃት የሚያጠናቅቁ ተሳታፊዎች የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ይሰጣቸዋል፡፡ አስፈላጊ ሁኔታዎቹ በሁሉም የስልጠና ቀናት ሙሉ ተሳትፎ ማድረግ እና የተለያዩ የሚሰጡ ስራዎችን በብቃትና በስኬት ማጠናቀቅን ያካትታል፡፡            

  • +251-115-571-150
  • Cette adresse e-mail est protégée contre les robots spammeurs. Vous devez activer le JavaScript pour la visualiser.
© 2022. All Rights Reserved. EDC-Ethiopia

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.