የሴቶች የንግድ ስራ ፈጠራ ስልጠናይህ ስልጠና ሴቶች የንግድ ስራ ባለቤት በመሆን ስራቸውን በማስኬድ ሂደት ውስጥ የሚገጥሟቸውን ተጨማሪ የኃላፊነት ጫና በመገንዘብ ሴቶችን ለማገዝና በሴቶች መሃከል የንግድ ስራ ፈጠራን ለማስተዋወቅ ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና ነው፡፡ ይህ የሴቶች የንግድ ስራ ፈጠራ ስልጠና ውስን የንግድ ስራ ልምድ እና/ወይም በጀማሪ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሴት የንግድ ስራ ፈጣሪዎች ላይ ትኩረት ያደረገ የሁለት ሙሉ ቀናት ስልጠና ነው፡፡

ስልጠናው ተሳታፊዎችን የግላዊ የንግድ ስራ ፈጠራ ብቃቶች እንዲያዳብሩ ከማድረግ በተጨማሪ ሰልጣኞች የንግድ ስራ በመስራት ሂደት ውስጥ ያላቸውን ውስጣዊ መተማመን መጨመር የሚያስችሏቸውን ክህሎቶች እንዲያዳብሩ ማስቻል ተጨማሪ ዓላማው ነው፡፡ በተጨማሪም ስልጠናው ሴት የንግድ ስራ ፈጠራ ሰዎች የሚገጥሟቸውን እንቅፋቶች ይዳስሳል፡፡ እንዲሁም እንቅፋቶቹን መወጣት የሚያስችሉ የመፍትኄ ሃሳቦች ላይ ውይይት ይደረጋል፡፡

ይህ ስልጠና ከኢ.ቲ.ደብሊው ተወስዶ በልዩ መልክ የተዘጋጀ እንደመሆኑ የሴት የንግድ ስራ ፈጠራ ሰዎች ፍላጎት ጋር በሚያስማማ መልኩ በኢ.ቲ.ደብሊው ስልጠና ላይ የሚተገበሩ የማሰልጠኛ ዘዴዎች ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡በመሆኑም  ይህ በልዩ መልክ የተዘጋጀው ስልጠና የአዋቂ ሰዎች የመማር መርሆች ላይ መሰረት ያደረገ ተሳታፊ ተኮር፣ ተግባራዊ፣ የአመለካከትና የባህሪ ለውጥ የሚያመጣ ስልጠና ነው፡፡ አብዛኛው የስልጠና አካሄድ በተለያዩ ጥናቶች፣ በትምህርታዊ ጨዋታዎች፣ በሮል ፕሌይ፣ በልምምዶችን እና በልምድ መለዋወጫ መንገዶች አማካይነት የሚሰጥ ነው፡፡

በስልጠናው የሚጠበቅባቸውን አስፈላጊ ሁኔታዎች በብቃት የሚያጠናቅቁ ተሳታፊዎች የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ይሰጣቸዋል፡፡ አስፈላጊ ሁኔታዎቹ በ2ቱ የስልጠና ቀናት ሙሉ ተሳትፎ ማድረግ እና የተለያዩ የሚሰጡ ስራዎችን በብቃትና በስኬት ማጠናቀቅን ያካትታል፡፡             • +251-115-571-150
  • Cette adresse e-mail est protégée contre les robots spammeurs. Vous devez activer le JavaScript pour la visualiser.
© 2022. All Rights Reserved. EDC-Ethiopia

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.