የገጠር የንግድ ስራ ፈጠራ ስልጠና


የገጠር የንግድ ስራ ፈጠራ ስልጠና በገጠር አካባቢዎች የሚገኙ በአነስተኛ ደረጃ ላይ ያሉ የንግድ ስራዎችን የሚሰሩ የንግድ ስራ ፈጠራ ሰዎች የንግድ ስራን የማቋቋም፣ ባለቤት የመሆን እንዲሁም የንግድ ስራውን የማስኬድ የንግድ ስራ ፈጠራ እና የንግድ ስራ ክህሎታቸውን እንዲያሻሽሉ ለማገዝ የተዘጋጀ የ3 ቀናት ስልጠና ነው፡፡ በገጠር አካባቢዎች የሚኖሩ የህብረተሰቡ አካላት በአካባቢያቸው ያሉ የንግድ ስራ ፈጠራ መልካም አጋጣሚዎችን መጠቀም እንዲችሉ እና አዎንታዊ የንግድ ስራ ፈጠራ አመለካከትና ተግባራዊ እርምጃ እንዲወስዱ ማገዝን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ስልጠናው በግብርናው ዘርፍ እሴት መጨመር ላይ እና  በተለያዩ የግብርና ምርቶች የእሴት ሰንሰለት ማለትም እንደ ሰብል ማምረት፣ ከብት እርባታ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እና ሌሌች የሰእሴት ሰንሰለቶች ውስጥ የሚገኙ የንግድ ስራ ፈጠራ መልካም አጋጣሚዎችን መፈለግ ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡

የገጠር የንግድ ስራ ፈጠራ ስልጠና የአዋቂ ሰዎች የመማር መርሆች ላይ መሰረት ያደረገ ተሳታፊ ተኮር፣ ተግባራዊ፣ የአመለካከትና የባህሪ ለውጥ የሚያመጣ ስልጠና ነው፡፡ አብዛኛው የስልጠና አካሄድ በተለያዩ ጥናቶች፣ በትምህርታዊ ጨዋታዎች፣ በሮል ፕሌይ፣ በልምምዶችን እና በልምድ መለዋወጫ መንገዶች አማካይነት የሚሰጥ ነው፡፡        

በስልጠናው የሚጠበቅባቸውን አስፈላጊ ሁኔታዎች በብቃት የሚያጠናቅቁ ተሳታፊዎች የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ይሰጣቸዋል፡፡ አስፈላጊ ሁኔታዎቹ በ3ቱ የስልጠና ቀናት ሙሉ ተሳትፎ ማድረግ እና የተለያዩ የሚሰጡ ስራዎችን በብቃትና በስኬት ማጠናቀቅን ያካትታል፡፡              • +251-115-571-150
  • Cette adresse e-mail est protégée contre les robots spammeurs. Vous devez activer le JavaScript pour la visualiser.
© 2022. All Rights Reserved. EDC-Ethiopia

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.