የወጣቶች የንግድ ስራ ፈጠራ ስልጠና
የወጣቶች የንግድ ስራ ፈጠራ ስልጠና የግላቸውን የንግድ ስራ መጀመር ለሚያስቡ ወጣቶች የተዘጋጀ የሁለት ቀናት ስልጠና ነው፡፡ ስልጠናው ተሳታፊዎች የንግድ ስራ ፈጠራ አመለካከትን እንዲያዳብሩ ያነሳሳል ያበረታታል፡፡
ስልጠናው ወጣቶች የንግድ ስራ ፈጠራን የሚታይ የህይወት ስራ አማራጭ አድርገው እንዲወስዱት የሚያበረታታ ጠንካራ የሆነ ፍላጎትን የሚያነሳሳ መርሃግብር ነው፡፡ ሰልጣኞች የንግድ ስራ ሃሳብ ማመንጨት መልካም አጋጣሚዎችን መለየት እና የንግድ ስራ እቅድ አወጣጥን የመሳሰሉ መሰረታዊ የንግድ ስራ ክህሎቶችን እንዲለማመዱ ያግዛል፡፡
በስልጠናው የሚጠበቅባቸውን አስፈላጊ ሁኔታዎች በብቃት የሚያጠናቅቁ ተሳታፊዎች የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ይሰጣቸዋል፡፡ አስፈላጊ ሁኔታዎቹ በ2ቱ የስልጠና ቀናት ሙሉ ተሳትፎ ማድረግ እና የተለያዩ የሚሰጡ ስራዎችን በብቃትና በስኬት ማጠናቀቅን ያካትታል፡፡