የሰራተኞች የንግድ ስራ ፈጠራ / ኢንትራፕርነርሺፕ (ኮርፖሬት ኢንተርፕርነርሺፕ)ትልልቅ ድርጅቶች ተፎካካሪ የንግድ ስልቶችን እንዲያጎለብቱና ግባቸውን እንዲያሳኩ ለማገዝ የንግድ ስራ ፈጠራ አመለካከት ያላቸው የድርጅት አስተዳዳሪዎች እና ዋና ስራ አስኪያጆች (ኢንትራፕርነርስ) አስፈላጊነት እየጨመረ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ይህ ስልጠና በከፍተኛ እና በመካከለኛ የአመራር ደረጃ ላይ በመንግስታዊ፣ በግል፣ እና በመንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ስራ አስኪያጆችን ምርታማነት ከፍ ለማድረግ ተቀርጾ የተዘጋጀ የ6 ቀናት የስልጠና መርሃግብር ነው፡፡ ይህ ስልጠና ስራ አስኪያጆች እንደ ስራ ፈጣሪ ሰዎች እንዲያስቡና በመስሪያ ቤታቸው ውስጥ ቀጣይነት ያለው ፈጠራዊ ማሻሻያዎችን እንዲያስተዋውቁ ለማገዝ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡  

ስልጠናው የአዋቂ ሰዎች የመማር መርሆች ላይ መሰረት ያደረገ ተሳታፊ ተኮር፣ ተግባራዊ፣ የአመለካከትና የባህሪ ለውጥ የሚያመጣ ስልጠና ነው፡፡ አብዛኛው የስልጠና አካሄድ በተለያዩ ጥናቶች፣ በትምህርታዊ ጨዋታዎች፣ በሮል ፕሌይ፣ በልምምዶችን እና በልምድ መለዋወጫ መንገዶች አማካይነት የሚሰጥ ነው፡፡

በስልጠናው የሚጠበቅባቸውን አስፈላጊ ሁኔታዎች በብቃት የሚያጠናቅቁ ተሳታፊዎች የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ይሰጣቸዋል፡፡ አስፈላጊ ሁኔታዎቹ በሁሉም የስልጠና ክፍለ ጊዜያት ሙሉ ተሳትፎ ማድረግ እና የተለያዩ የሚሰጡ ስራዎችን በብቃትና በስኬት ማጠናቀቅን ያካትታል፡፡            

  • +251-115-571-150
  • Cette adresse e-mail est protégée contre les robots spammeurs. Vous devez activer le JavaScript pour la visualiser.
© 2022. All Rights Reserved. EDC-Ethiopia

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.