የንግድ ስራዎች ማበልጸጊያ(ኢንኩቤሽን)

የወጣት ባለ ተሰጥዖችን የንግድ ስራ ፈጠራ ለማበረታታት ብሎም ለማስፋፋት የሚያስችሉ፣ ለገበያ እንዲቀርቡ ብቁ ለማድረግ እንዲሁም በስተመጨረሻ አዳዲስ የንግድ ስራዎችን በመገንባት እና በኢትዮጵያ የስራ ዕድል መፍጠር የሚያስችሉ ፈጠራን እና የመዋዕለ ነዋይ ፍሰትን (ኢንቨስትመንት) ለመሳብና ለማበረታታት (ለማስተዋወቅ) ከምንሰራቸው የኢ.ዲ.ሲ ዋና የስራ ክፍል አንዱ የንግድ ስራዎች ማበልጸጊያ ክፍል ነው፡፡    

 

አቅርቦቶች  

  • የመረጃ ቴክኖሎጂ በይነ መረብ (ኢንተርኔት) እና የመስሪያ ቦታ አቅርቦት         
  • ከተለያዩ የፈጠራ ስራ ባለቤትነት መረጃዎች በተጨማሪ ልዩ የፈጠራ ስራ ባለቤትነት መረጃ (ኤ.ኤስ.ፒ.አይ) አቅርቦት እና የዕድገትና ፈጠራ ጥናት (ኤ.አር.ዲ.አይ)
  • የፈጠራ ስራ ሽልማቶችን፣ የገንዘብ ድጋፎችን እንዲሁም የእገዛ አገልግሎቶችን የሚመለከቱ መረጃዎች አቅርቦት
  • ለንግድ ስራ ፈጣሪዎች የንግድ ስራ ዕቅድ ማዘጀት፣ የገንዘብ ነክ ጉዳዮች ማስተዳደር፣ መረጃ መቀበልና ሌሎች ሃብቶችን መጠቀም የሚያስችሉ ፈጠራ ነክ የመረጃ ማግኛ መፍትሄዎችን ማቅረብ
  • እንደ የጊዜ አጠቃቀም፣ የስራ ስነ-ምግባር፣ የቡድን ስራ፣ የደንበኛ አገልግሎት የመሳሰሉ ክህሎቶችን የሚያስጨብጡ ስልጠናዎች
  • የልምድ እና የዕውቀት ማጋሪያ(ማካፈያ) እና ንግድ ስራ ትስስር መፍጠር ሚያስችሉ መድረኮች
  • ፈጠራን ማስተዋወቂያና ትስስር መፍጠሪያ መንገዶች - የሙያዊ እገዛ/የቤተ-ሙከራ/የመስሪያ አቅርቦት፣ የገንዘብ ነክ መልካም አጋጣሚዎችን፣ እና የፈጠራ ስራ ባለቤትነት ማግኛ ህጎችን እንዲሁም የንግድ ስራ መስሪያ ቦታ ማግኘት የሚያስችሉ አካላት ጋር ትስስር መፍጠር የሚያስችሉ አገልግሎቶችን ማቅረብ፡፡ በበይነ መረብ ድረ-ገፅ (ዌብሳይት) አማካይነት የፈጠራ ስራዎችንና የፈጠራ ስራ ባለቤቶችን ማንነት የማስተዋወቅ ስራ መስራት፡፡ በግብይት ትርዒት ማሳያ ባዛሮች አማካይነት የገበያ ትስስር መፍጠር፡፡ በአጋርነት መስራት እና የገበያ ትስስር መፍጠርያ መልካም አጋጣሚዎች ማመቻቸት፡፡       
  • +251-115-571-150
  • Cette adresse e-mail est protégée contre les robots spammeurs. Vous devez activer le JavaScript pour la visualiser.
© 2022. All Rights Reserved. EDC-Ethiopia

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.