የወረቀት ኢንዱስትሪውን ለመለወጥ የምትፈልገው ኢትዮጵያዊት የንግድ ስራ ፈጣሪ

Vote utilisateur: 3 / 5

Etoiles activesEtoiles activesEtoiles activesEtoiles inactivesEtoiles inactives
 

ቤተልሔም ደጀኔ አበበ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመርያ ዓመት የትምህርት ቆይታዋ በኢትዮጵያ ትልቁን የአትክልትና ፍራፍሬ ገበያ የሆነውን አትክልት ተራን ከእናቷ ጋር በመሆን ጎበኘች፡፡ በገበያው ያለው ሁኔታበጣም አስደነገጣት፡፡ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዐት በሚመለከት በቆራጥነት መስራት እንዳለባት እንትወሰን አደረጋት፡፡  

“በጣም በሚያስገርም ሁኔታ ቆሻሻ ነበር፡፡ በጣም መጥፎ ሽታ ይሸታል፡፡ ፈጽሞ ጤናማ አልነበረም” ትላለች፡፡ “በዚያ ወቅት ነበረ ለውጥ ለማምጣት አንድ ነገር መሞከር እንዳለብኝ የወሰንኩት፡፡”     


ቤተልሔም 100% ከዛፍ ነጻ የሆነ ከግብርና ተረፈ ምርት የሚሰራ የወረቀት ፐልፕ (ወረቀት መስሪያ) ያስተዋወቀው የዛፍሪ ፔፐርስ የጋራ መስራችና የስራ አስፈጻሚ ነች፡፡ ዛፍሪ ፔፐርስ የወረቀት መስሪያን ለመስራት እንጨትን ከመጠቀም ይልቅ አርሶአደሮች የአየር ብክለትን የሚያስከትለውን ተረፈ ምርት ከማቃጠል በመከላከል የስንዴና የገብስ ሰንበሌጥ ሳርን ወረቀት ለማምረት ይጠቀማል፡፡ የድርጅቱ የመስሪያ ቦታ አሁን ላይ ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ሰሜን-ምስራቅ 120 ኪ.ሜ በደብረብርሃን ከተማ እየተገነባ ይገኛል (የበለጠ ለማንበብ፡ City on the move: Debre Berhan, Ethiopia) ፡፡ በራሷ አንደበት እንደምትገልፀው ዛፍሪ ፔፐርስ አሁን ላይ ያለበት ደረጃ ላይ ለመድረስ የመጣበት መንገድ ቀላል አልነበረም፡፡ በጣም ፈታኝ ነበረ፡፡ “የወደቅኩባቸው ጊዜያት ቁጥር ምን ያህል እንደነበሩ የረሳሁት ይመስለኛል” ትላለች፡፡          

ከንድፈ ሃሳብ ወደ ንግድ ስራ ዕቅድ


ከገበያ ስፍራው ጉብኝት ጀምሮ የቤተልሔም አዕምሮ ውስጥ ያሉትን ዓላማዎች መድረስ ያልቻሉ የተወሰኑ ሙከራዎች ነበሩ፡፡ “ነገር ግን አንድ በር ሲዘጋ ሌላው ይከፈታል ብዬ አምናለሁ፡፡ አንድ ውድቀት ወደ ሌላ ስኬት ያመራል” ትላለች፡፡  

በመጀመርያ ከራሷ መኖሪያ ቤት የወጡ ወረቀት ቆሻሻ ተረፈ ምርቶችን ብቻ ወደ ምርትነት ቀየረች፡፡ ከዚያም የተረፈ ምርቱን ማምረት ስራ የበለጠ ለገበያ ወደሚቀርብ የንግድ ስራነት እንዴት ማሳደግ እንደሚቻል ምርምር ማድረግ ጀመረች፡፡ በመጨረሻም የተረፈ ምርትን ወደ ምርትነት ከመቀየር ስራ ወደ - ለወረቀት አምራቾች ሊቀርብ የሚችል የመጨረሻውን ምርት ጥራት በማይቀንስ የግብርና ተፈረ ምርትን በመጠቀም ከእንጨት-ነፃ ወረቀት መስሪያ ማምረት ስራ ለመሄድ ወሰነች፡፡  

ከዚያም የሰዎችን በር የማንኳኳ ስራው መጣ፡፡ “ሁሉንም በሮች አንኳኩቻለሁ” - ሳቅ፡፡ “በኢትዮጵያ ከ20 በላይ የግል ባንኮች አሉን፡፡ ምንም ዕውቀቱ ሳይኖረኝ ምንም ማስያዣ ሳይኖረኝ ብድር ለመጠየቅ ብቻ ሁሉም ጋር ሄጃለሁ፡፡” 

Bethelhem Dejene Abebe

 

ቶፊ ከግሉተን ነፃ ኬክ

መጨረሻም ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የፕሮጀክት ገንዘብ አገኘች እናም በደብረብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ መሬት አገኘች፡፡ ከእርሷ የሚጠበቀው 25% የባለቤት መዋጮ ነበር፡፡ “በዚያ ደረጃ ኢንቨስተር ምንእንደሆነ እንኳን አላውቅም ነበር” ትላለች፡፡

በመቀጠል ጓደኞቿ ቤተልሔምን በአንተርፕርነርሺፕ ልማት ማዕከል - ኢትዮጵያ (ኢ.ዲ.ሲ) የሚሰጠውን የንግድ ስራ ፈጠራ ስልጠናን (የአንተርፐርርነርሺፕ ስልጠና ወርክሾፕ - ኢ.ቲ.ደብሊው) እንድትወስድ መከሯት፡፡ “ይህ ለእኔ ወሳኝ የለውጥ ምዕራፍ ነበር፡፡ ስለ ንግድ ስራ ፈጠራና መደረግ ስላለባቸውና ስለሌለባቸው ጉዳዮች ተማርኩ፡፡ እንዲሁም የግሌን የንግድ ስራ ለመጀመር እና የገንዘብ ድጋፍ ለማሰባሰብ የሚያስችሉ መንገዶችን ያሳዩኝ ብዙ ሰዎችን ተዋወቅሁኝ” ትላለች፡፡         


Mario Manicureaux

“በዚያ ደረጃ ኢንቨስተር ምንእንደሆነ እንኳን አላውቅም ነበር” ትላለች፡፡ በመቀጠል ጓደኞቿ ቤተልሔምን በአንተርፕርነርሺፕ ልማት ማዕከል - ኢትዮጵያ (ኢ.ዲ.ሲ) የሚሰጠውን የንግድ ስራ ፈጠራ ስልጠናን (የአንተርፐርርነርሺፕ ስልጠና ወርክሾፕ - ኢ.ቲ.ደብሊው) እንድትወስድ መከሯት፡፡ “ይህ ለእኔ ወሳኝ የለውጥ ምዕራፍ ነበር፡፡ ስለ ንግድ ስራ ፈጠራና መደረግ ስላለባቸውና ስለሌለባቸው ጉዳዮች ተማርኩ፡፡ እንዲሁም የግሌን የንግድ ስራ ለመጀመር እና የገንዘብ ድጋፍ ለማሰባሰብ የሚያስችሉ መንገዶችን ያሳዩኝ ብዙ ሰዎችን ተዋወቅሁኝ” ትላለች፡፡           

 

  

ቤተልሔም ደጀኔ አበበ

  • +251-115-571-150
  • Cette adresse e-mail est protégée contre les robots spammeurs. Vous devez activer le JavaScript pour la visualiser.
© 2022. All Rights Reserved. EDC-Ethiopia

We use cookies to improve your experience on our website. By browsing this website, you agree to our use of cookies.