ኤልሳቤት ትባላለች፡፡ ስራ ፈጣሪ፣ አርቲስት፣ ዲዛይነር እና መምህርት ናት፡፡ እስካሁን ድረስ ተንቀሳቃሽ የመፀዳጃ ሽንት ቤቶችንና የፕላስቲክ ክዳን ስራዎችን ጨምሮ ከ7 በላይ የፈጠራ ስራዎችን ሰርታለች፡፡

በቅርቡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀሰቀሰውን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከለካከል ለማገዝ ለጤናዎ የሚረዱ የፕላስቲክ ዘይት እና የማከሚያ ፈሳሽ ሳሙና በመጠቀም የወንዶችና የሴቶች የእጅ ቦርሳዎችን ሰርታ አምርታለች፡፡ ቦርሳዎቹ የአፍና አፍንጫ ማስኮችን፣ የእጅ ማፅጃዎችን፣ አልኮል፣ ውሃ፣ ሳሙና እና ፎጣዎችን በውስጣቸው ይይዛሉ፡፡ ይህ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይም ለድሆች የቀረበ ነው፡፡ አሁን ላይ ምን የፈጠራ ስራ እየሰራችሁ ነው? አስቡ፣ ጥናት አድርጉ፣ የማህበረሰባችንን ችግር ፍቱ!