ጌታቸው ገ/ህይወት ራሱን የቀየረ ስራ ፈጣሪና የጌታቸውና ይብራለም በአዕምሮ ንብረት የተመዘገበ የፈጠራ ምህንድስና ባለቤት ነው፡፡ ከአምስት ዓመታት በፊት ንጽህናውን የጠበቀ የህሙማን አልጋ ብሎ የሰየመውን አልጋ የእንጀራ አባቱን ለመደገፍ ሲል ፈጥሮ ሰራ፡፡
ይህ ፈጠራ የኣካል ጉዳት ያለባቸውን ሰዎች፣ የአረጋውያንን እና የነፍሰ ጡር ሴቶችን የቀን ተቀን እንቅስቃሴዎች ሊያቀሉ የሚችሉ አጋዥ መገልገያዎችን ለምሳሌ ተንቀሳቃሽ ሽንት ቤት፣ ተንቀሳቃሽ ገላ መታጠብያ፣ ተለጣጭ ወንበር፣ ተሽከርካሪ ወንበሮች እና የህሙማን አልጋ ከተንቀሳቃሽ የንጽህና መጠበቂያ ዘዴዎችን መፍጠር ላይ እንዲያተኩር አነሳሳው፡፡ በቅርቡ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚረዳ አዲስ ፈጠራ ጋር መጥቷል፡፡ አንድአንድ የፈጠራ ስራዎቹ በእግር እንቅስቃሴ የሚሰራ እጅ መታጠብያ፣ ተንቀሳቃሽ የሽንት ቤት ጉድጓድ፣ የበድን ከካላት ማጠብያ ሳህንን ያካትታሉ፡፡.
የህዝብ ሆስፒታሎች እና የኮቪድ ማገገሚያ ማዕከላት የምርቶቹ ዋና ደንበኛች ናቸው፡፡ ጌታቸውና ይብራለም በአዕምሮ ንብረት የተመዘገበ የፈጠራ ምህንድስና ከ8 በላይ ቋሚ የስራ እድሎችን ፈጥሯል፡፡ የፈጠራ ባለቤቶችን እንቅፋቶች በማቃለል አገር በቀል የፈጠራ መፍትሔዎችን እናስተዋውቅ፡፡